...

Amharic Quran

ኑህ

بسم الله الرحمن الرحيم

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

71:1

እኛ ኑሕን «ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው፡፡»

🔊 📋 🔍
71:2

(እርሱም) አለ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ ገላጭ የኾንኩ አስጠንቃቂ ነኝ፡፡

🔊 📋 🔍
71:3

«አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ ታዘዙኝም በማለት፤ (አስጠንቃቂ ነኝ)፡፡

🔊 📋 🔍
71:4

«ለእናንተ ከኀጢኣቶቻችሁ ይምራልና፡፡ ወደተወሰነው ጊዜም ያቆያችኋል፡፡ የአላህ (የወሰነው) ጊዜ በመጣ ወቅት አይቆይም፡፡ የምታውቁት ብትኾኑ ኖሮ (በታዘዛችሁ ነበር)፡፡»

🔊 📋 🔍
71:5

(ስለ ተቃወሙትም) «አለ ጌታዬ ሆይ! እኔ ሌሊትም ቀንም ሕዝቦቼን ጠራሁ፡፡

🔊 📋 🔍
71:6

«ጥሪየም መሸሽን እንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም፡፡

🔊 📋 🔍
71:7

«እኔም ለእነርሱ ትምር ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ፡፡ ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ፡፡

🔊 📋 🔍
71:8

«ከዚያም እኔ በጩኸት ጠራኋቸው፡፡

🔊 📋 🔍
71:9

«ከዚያም እኔ ለእነርሱ ገለጽኩ፡፡ ለእነርሱም መመስጠርን መሰጠርኩ

🔊 📋 🔍
71:10

«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡

🔊 📋 🔍
71:11

«በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡

🔊 📋 🔍
71:12

«በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»

🔊 📋 🔍
71:13

ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለእናንተ ምን አላችሁ?

🔊 📋 🔍
71:14

በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን፡፡

🔊 📋 🔍
71:15

አላህ ሰባትን ሰማያት አንዱ ካንዱ በላይ ሲኾን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?

🔊 📋 🔍
71:16

በውስጣቸውም ጨረቃን አብሪ አደረገ፡፡ ፀሐይንም ብርሃን አደረገ፡፡

🔊 📋 🔍
71:17

አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ፡፡

🔊 📋 🔍
71:18

ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል፡፡ ማውጣትንም ያወጣችኋል፡፡

🔊 📋 🔍
71:19

አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት፡፡

🔊 📋 🔍
71:20

ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ፡፡

🔊 📋 🔍
71:21

ኑሕ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እነሱ አምመጹብኝ፡፡ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ፡፡

🔊 📋 🔍
71:22

«ታላቅንም ተንኮል የመከሩትን ሰዎች» (ተከተሉ)፡፡

🔊 📋 🔍
71:23

አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡

🔊 📋 🔍
71:24

«በእርግጥም ብዙዎችን አሳሳቱ፡፡ ከሓዲዎችንም ጥመትን እንጅ ሌላን አትጨምርላቸው» (አለ)፡፡

🔊 📋 🔍
71:25

በኀጢኣቶቻቸው ምክንያት ተሰጠሙ፡፡ እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የኾኑ ረዳቶችን አላገኙም፡፡

🔊 📋 🔍
71:26

ኑሕም አለ «ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው፡፡

🔊 📋 🔍
71:27

«አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና፡፡ ኀጢኣተኛ ከሓዲንም እንጅ ሌላን አይወልዱም፡፡

🔊 📋 🔍
71:28

«ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ምእመን ኾኖ በቤቴ ለገባም ሰው ሁሉ ለምእመናንና ለምእምናትም ምሕረት አድርግ፡፡ ከሓዲዎችንም ከጥፋት በቀር አትጨምርላቸው፤» (አለ)፡፡

🔊 📋 🔍
00:00 / 00:00
Seraphinite AcceleratorOptimized by Seraphinite Accelerator
Turns on site high speed to be attractive for people and search engines.